1. እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
2. ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
3. ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ። ሴላ
4. የልብህን መሻት ይስጥህ፤ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።
5. በአንተ ድል ደስ ይበለን፤በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6. እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድንአሁን ዐወቅሁ፤የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።