መዝሙር 18:43-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. ከሕዝብ ግርግር አወጣኸኝ፤የሕዝቦች መሪ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፤የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ።

44. ትእዛዜን እንደ ሰሙ ይታዘዙልኛል፤ባዕዳንም በፊቴ አንገት ደፉ።

45. ባዕዳን በፍርሃት ተዋጡ፤ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።

46. እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐምባዬ ይባረክ፤ያዳነኝ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።

መዝሙር 18