መዝሙር 18:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጒልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድሃለሁ።

2. እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።

3. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ።

4. የሞት ገመድ አነቀኝ፤የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።

5. የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።

6. በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ።

7. ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤ጌታ ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።

8. ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤የሚባላ እሳት ከአፉ፤የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ።

9. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቍር ደመና ነበረ።

መዝሙር 18