መዝሙር 18:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጒልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድሃለሁ።

2. እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።

3. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ።

4. የሞት ገመድ አነቀኝ፤የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።

5. የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።

መዝሙር 18