መዝሙር 148:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።

6. ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7. የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

8. እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

መዝሙር 148