መዝሙር 148:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት።

4. ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።

5. እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።

6. ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7. የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

መዝሙር 148