7. ለተበደሉት የሚፈርድ፣ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
8. እግዚአብሔር የዕዉራንን ዐይን ያበራል፤ እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወዳል፤
9. እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
10. እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው።ሃሌ ሉያ።