1. ሃሌ ሉያ።ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
2. በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርንአመሰግናለሁ፤በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3. በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ።
4. መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።
5. ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤
6. እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤
7. ለተበደሉት የሚፈርድ፣ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
8. እግዚአብሔር የዕዉራንን ዐይን ያበራል፤ እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወዳል፤
9. እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።