መዝሙር 145:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በየቀኑ እባርክሃለሁ፤ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3. እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ታላቅነቱም አይመረመርም።

4. ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

5. ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።

መዝሙር 145