መዝሙር 145:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

19. ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

20. እግዚአብሔር የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21. አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።

መዝሙር 145