መዝሙር 145:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።

2. በየቀኑ እባርክሃለሁ፤ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3. እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ታላቅነቱም አይመረመርም።

4. ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

መዝሙር 145