መዝሙር 139:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. መሄድ መተኛቴን አጥርተህ ታውቃለህ፤መንገዶቼንም ሁሉ ተረድተሃቸዋል።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ፣እነሆ፤ አንተ ሁሉንም ታውቃለህ።

5. አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ፤እጅህንም በላዬ አደረግህ።

6. እንዲህ ያለው ዕውቀት ለኔ ድንቅ ነው፤ልደርስበትም የማልችል ከፍ ያለ ነው።

7. ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?

መዝሙር 139