መዝሙር 138:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤በአማልክት ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ።

2. ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ስምህንና ቃልህን፣ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3. በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።

መዝሙር 138