መዝሙር 129:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።

5. ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

6. ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤

7. ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።

8. መንገድ ዐላፊዎችም፣“የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።

መዝሙር 129