መዝሙር 118:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

11. መክበቡንስ በየአቅጣጫው ከበቡኝ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

12. እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤ነገር ግን እንደሚነድ እሾኽ ከሰሙ፤በእርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

13. ተገፍትሬ ልወድቅ ተንገደገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን ረዳኝ።

14. እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤አዳኝ ሆነልኝ።

መዝሙር 118