መዝሙር 115:6-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤

7. እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤በጒሮሮአቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።

8. እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።

9. የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

10. የአሮን ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

11. እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

12. እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንንም ቤት ይባርካል።

13. እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።

14. እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣በባርኮቱ ያብዛችሁ።

15. ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።

16. ሰማየ ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው፤ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።

17. እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑት የሞቱት አይደሉም፤ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱም አይደሉም።

18. ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔርን የምንባርክ እኛ ነን። እግዚአብሔር ይመስገን።

መዝሙር 115