መዝሙር 113:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

8. ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።

9. መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።ሃሌ ሉያ።

መዝሙር 113