መዝሙር 112:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።

3. ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።

4. ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።

5. ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤

6. ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።

7. ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

8. ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።

መዝሙር 112