መዝሙር 109:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።

5. በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።

6. ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ከሳሽም በቀኙ ይቁም።

7. ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።

8. ዕድሜው ይጠር፤ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው።

መዝሙር 109