መዝሙር 109:3-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በጥላቻ ቃል ከበውኛል፤ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል።

4. ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።

5. በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።

6. ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ከሳሽም በቀኙ ይቁም።

7. ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።

8. ዕድሜው ይጠር፤ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው።

9. ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ሚስቱም መበለት ትሁን።

10. ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።

11. ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።

12. ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

13. ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

14. የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።

መዝሙር 109