መሳፍንት 9:32-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ስለዚህ በሌሊት ሰዎችህን ይዘህ ወጥተህ ሜዳው ላይ ማድፈጥ አለብህ፤

33. ጠዋት ፀሓይ ስትወጣም ወደ ከተማዪቱ ገሥግሥ፤ ገዓልና ሰዎቹ ሊገጥሙህ በሚወጡበት ጊዜ እጅህ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርግ።

34. ስለዚህ አቤሜሌክና ሰዎቹ በሙሉ በሌሊት ወጡ፤ በአራት ምድብ ሆነውም በሴኬም አጠገብ አደፈጡ።

35. የአቤድ ልጅ ገዓል ከከተማዪቱ ወጥቶ በመግቢያው በር ላይ ሲቆም፣ አቤሜሌክና ሰዎቹ ካደፈጡበት ወጡ።

36. ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው።ዜቡልም መልሶ፣ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ” ነው አለው።

መሳፍንት 9