26. “ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ እንዲህም በላቸው፤“መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ማየትን ታያላችሁ፤ ነገር ግን አትመለከቱም።”
27. የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና፤ጆሮአቸውም ተደፍኖአል፤ዐይናቸውንም ጨፍነዋል።አለዚያማ፣ በዐይናቸው አይተው፣በጆሮአቸው ሰምተው፣በልባቸው አስተውለው፣ይመለሱና እፈውሳቸዋለሁ።’
28. “ስለዚህ የእግዚአብሔር ማዳን ለአሕዛብ እንደ ተላከ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ እነርሱም ይሰሙታል።”
29. ይህንንም ከተናገረ በኋላ፣ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።
30. ጳውሎስም ራሱ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደስታ ይቀበል ነበር፤
31. ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ፣ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ግልጽነት ያስተምር ነበር።