ሆሴዕ 8:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ጠላትም ያሳድዳቸዋል።

4. ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።

5. ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤የማይነጹት እስከ መቼ ነው?

6. ይህም በእስራኤል ሆነ!ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክአይደለም፤ያ የሰማርያ ጥጃ፣ተሰባብሮ ይደቃል።

7. “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።

8. እስራኤል ተውጠዋል፤በአሕዛብም መካከል፣ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።

ሆሴዕ 8