1. “መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ፤ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤
2. እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን’ እያሉ፣ወደ እኔ ይጮኻሉ።
3. ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ጠላትም ያሳድዳቸዋል።
4. ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።
5. ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤የማይነጹት እስከ መቼ ነው?
6. ይህም በእስራኤል ሆነ!ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክአይደለም፤ያ የሰማርያ ጥጃ፣ተሰባብሮ ይደቃል።