ሆሴዕ 7:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣የኤፍሬም ኀጢአት፣የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

2. ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣እነርሱ አይገነዘቡም፤ኀጢአታቸው ከቦአቸዋል፤ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።

3. “ንጉሡን በክፋታቸው፣አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።

4. ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣እንደሚነድ ምድጃ፣ሁሉም አመንዝራ ናቸው።

ሆሴዕ 7