ሆሴዕ 6:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔርን እንወቀው፤የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤እንደ ንጋት ብርሃን፣በእርግጥ ይገለጣል፤ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”

4. “ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።

5. ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።

ሆሴዕ 6