1. “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤እርሱ ሰባብሮናል፤እርሱም ይጠግነናል፤እርሱ አቊስሎናል፤እርሱም ይፈውሰናል።
2. ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል፤በእርሱም ፊት እንድንኖር፣በሦስተኛው ቀን ያስነሣናል።
3. እግዚአብሔርን እንወቀው፤የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤እንደ ንጋት ብርሃን፣በእርግጥ ይገለጣል፤ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
4. “ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።
5. ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።
6. ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና።