ሆሴዕ 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ክስ ስላለው፣እናንት እስራኤላውያን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤“ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።

2. በዚያ ያለው ርግማን፣ መዋሸት፣ መግደል፣መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።

3. ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣የባሕርም ዓሦች አለቁ።

ሆሴዕ 4