ሆሴዕ 13:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. “እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።

10. “ንጉሥንና አለቆችን ስጠኝ፤”ብለህ እንደ ጠየቅኸው፣ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ የት አለ?በከተሞችህ ሁሉ የነበሩ ገዦችህስ የት አሉ?

11. በቊጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤በመዓቴም ሻርሁት።

12. የኤፍሬም በደል ተከማችቶአል፤ኀጢአቱም በመዝገብ ተይዞአል።

13. በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።

ሆሴዕ 13