2 ዜና መዋዕል 6:38-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. ተማርከው በሚኖሩበትም ምድር ሆነው በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹምም ነፍሳቸው ቢመለሱና ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር፣ አንተም ወደ መረጥኻት ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ቢጸልዩ፣

39. ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በሰማይ በማደሪያህ ስማ፤ የጠየቊህንም አድርግላቸው። የበደሉህንም የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር በል።

40. አሁንም አምላኬ ሆይ፤ በዚህ ስፍራ ወደ ቀረበው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ፣ ጆሮዎችህም የሚያደምጡ ይሁኑ።

2 ዜና መዋዕል 6