2 ዜና መዋዕል 17:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺ ተዋጊዎች ጋር፤

15. ከእርሱ ቀጥሎም አዛዡ የሆሐናን ከሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ጋር፤

16. ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺህ ተዋጊዎች ጋር፤

17. ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺ ሰዎች ጋር፤

18. ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ጋር፤

2 ዜና መዋዕል 17