1 ዜና መዋዕል 7:20-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የኤፍሬም ዘሮች፤ሹቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣

21. ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።

22. አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።

23. ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።

24. ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።

25. ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣

26. ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ልጁ ኤሊሳማ፣

27. ልጁ ነዌ፣ልጁ ኢያሱ።

28. ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም አልፎ ዓያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር።

29. በምና ሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነ መንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር።

30. የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።

1 ዜና መዋዕል 7