45. የሐሸብያ ልጅ፣የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣
46. የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣የሴሜር ልጅ፣
47. የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
48. ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
49. የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
50. የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ልጁ አልዓዛር፣ ልጁ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሱ
51. ልጁ ቡቂ፣ልጁ ኦዚ፣ ልጁ ዘራእያ፣
52. ልጁ መራዮት፣ ልጁ አማርያ፣ልጁ አኪጦብ፣
53. ልጁ ሳዶቅ፣ልጁ አኪማአስ።
54. መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።
55. ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የምትገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፤
56. በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ።