1. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።
2. ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የብኵርና መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።
3. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ።
4. የኢዩኤል ዘሮችልጁ ሸማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁሰሜኢ፣
5. ልጁ ሚካ፣ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣
6. የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ማርኮ የወሰደው ልጁ ብኤራ።
7. የቤተ ሰቡ የዘር ትውልድ በየጐሣ በየጐሣው ሲቈጠር እንደሚከተለው ነው፤የጐሣ አለቃ የሆነው ኢዮኤል፣ ዘካርያስ፣
8. የኢዮኤል ልጅ፣ የሽማዕ ልጅ፣ የዖዛዝ ልጅ ቤላ፣ እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።
9. ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለ ነበር በምሥራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።
10. በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።
11. የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤