31. የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሽዒ። ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕላይን ወለደ።
32. የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
33. የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ ዛዛ።እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
34. ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው።
35. ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓታይ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
36. ዓታይ ናታንን ወለደ፤ናታንም ዛባድን ወለደ፤
37. ዛባድ ኤፍላልን ወለደ፤ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
38. ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
39. ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ኬሌስ ኤልዓሣን ወለደ፤
40. ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
41. ሰሎም የቃምያን ወለደ፤የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
42. የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።
43. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።