1 ዜና መዋዕል 1:27-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።

28. የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ይስሐቅ፣ እስማኤል።

29. የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣

30. ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣

31. ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።

32. የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው።የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ሳባ፣ ድዳን።

33. የምድያም ወንዶች ልጆች፤ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፤እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።

34. አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤ዔሳው፣ እስራኤል።

35. የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።

36. የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም፣ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።

37. የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።

38. የሴይር ወንዶች ልጆች፤ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።

39. የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ሖሪ፣ ሄማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

1 ዜና መዋዕል 1