ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ስለ ተሸነፉ እያንዳንዱ ወደየድንኳኑ ሸሸ። ታላቅ እልቂት ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ወደቁ።