14. ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቊርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”
15. ሳሙኤል እስኪነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤
16. ዔሊ ግን ሳሙኤልን፣ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው።ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” ሲል መለሰ።
17. ዔሊም፣ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድ ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው።
18. ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ።
19. ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፣ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።