4. እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።
5. በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤
6. እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤
7. ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ራሱን ባዶ አደረገ፤
8. ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ራሱን ዝቅ አደረገ፤እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከመሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
9. ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤
10. ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣
11. ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
12. ስለዚህ፣ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤