ፊልጵስዩስ 2:27-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. በርግጥም ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ምሕረት አደረገለት፤ በሐዘን ላይ ሐዘን እንዳይደራረብብኝ፣ ለእኔም ጭምር እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም።

28. ስለዚህ እርሱን እንደ ገና ስታዩ ደስ እንዲላችሁና የእኔም ጭንቀት እንዲቀል ልልከው በጣም ጓጒቻለሁ።

29. በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፤ እንደ እርሱ ያሉትንም ሰዎች አክብሯቸው።

ፊልጵስዩስ 2