ዳንኤል 5:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ስለዚህ እርሱ ጽሕፈቱን የጻፈውን እጅ ላከ።

25. “የተጻፈውም ጽሕፈት፣‘ማኔ፣ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ” ይላል።

26. “የቃሉም ትርጒም ይህ ነው፤‘ማኔ’ ማለት እግዚአብሔር የመንግሥትህን ዘመን ቈጠረው፤ ወደ ፍጻሜም አደረሰው ማለት ነው።

27. ‘ቴቄል’ ማለት በሚዛን ተመዘንህ፤ ቀለህም ተገኘህ፣ ማለት ነው።

28. ‘ፋሬስ’ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።

ዳንኤል 5