ዳንኤል 5:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ንጉሥ ቤልሻዛር ለሺህ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር።

2. ቤልሻዛር የወይን ጠጁን እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቍባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ።

ዳንኤል 5