ዮናስ 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

2. እንዲህም አለ፤“ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤እርሱም መለሰልኝ፤ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤አንተም ጩኸቴን ሰማህ።

3. ጥልቅ ወደ ሆነው፣ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣በላዬ አለፉ።

ዮናስ 2