ዮሐንስ 6:68-71 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

68. ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤

69. አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል፤ ዐውቀናልም።”

70. ኢየሱስም መልሶ፣ “ዐሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኋችሁ እኔ አይደለሁምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው” አላቸው።

71. የአስቆሮቱ የስምዖን ልጅ ይሁዳ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም፣ ኋላ አሳልፎ ስለሚሰጠው ስለ እርሱ መናገሩ ነበር።

ዮሐንስ 6