ዮሐንስ 6:45-48 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. በነቢያትም፣ ‘ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፎአል፤ አብን የሚሰማና ከእርሱም የሚማር ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።

46. ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ አብን ያየው እርሱ ብቻ ነው።

47. እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው።

48. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።

ዮሐንስ 6