ዮሐንስ 18:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘እርሱ እኔ ነኝ’ ብያችኋለሁ እኮ፤ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ፣ እነዚህ ፣ ይሂዱ ተዉአቸው” አለ፤

9. ይህ የሆነው፣ “ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንድም አልጠፋብኝም” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።

10. ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስም፣ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮ ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ይባል ነበር።

11. ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ! አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣምን?” አለው።

12. ወታደሮቹም ከአዛዣቸውና ከአይሁድ ሎሌዎች ጋር በመሆን ኢየሱስን ያዙት፤ አስረውም፣

ዮሐንስ 18