8. ንጹሕ ከሆኑትና ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት፣ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ ጥንድ ጥንድ፣
9. ተባዕትና እንስት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ መርከቧ ገቡ።
10. ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።
11. ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤