ዘፍጥረት 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ።

2. ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ 3 ንጹህ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት

3. እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ።

4. ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።”

5. ኖኅም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።

6. የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር።

ዘፍጥረት 7