ዘፍጥረት 5:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው።

3. አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

4. ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤

5. አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

ዘፍጥረት 5