ዘፍጥረት 49:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።

17. ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።

18. “እግዚአብሔር ሆይ (ያህዌ)፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።

19. “ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።

20. “አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።

ዘፍጥረት 49